Tuesday, February 2, 2016

አንዳርጋቸው በምናቤ

ከተስፋዬ ገብረአብ

እነሆ! ቅዳሜ ዞሮ መጣ። በዚህች የቅዳሜ ምሽት ስለ አንዳርጋቸው ጥቂት አወጋ ዘንድ መንፈሴ መራኝ። አዲስ ነገር አትጠብቁ። ከቀንዱም ከሸኾናውም ዝም ብዬ አወጋለሁ። የምትሰሩት ሌላ አስቸኳይ ጉዳይ ካላችሁ ይህን ፅሁፍ ለማንበብ ጊዜአችሁን አታቃጥሉ። እንደው ዘና ብላችሁ ከሆነ ግን ብታነቡት ምንም አይላችሁም።

Wednesday, January 27, 2016

የአባይ ፀሃዬ ጦርነት

ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

ከኦሮሚያ አመፅ ጋር በተያያዘ አባይ ፀሃዬ ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል። አንዳንድ ደንፊ ንግግሮች መናገሩንም ስናነብ ሰነባብተናል። ምን እንደነካው እንጃ እንጂ ጠባዩ እንኳ እንዲያ አልነበረም። አባይ በጠባዩ ድመት መሆኑ ነበር የሚታወቀው። ሊያጠቃ ሲፈልግ እንደ ፈረስ ጋማህን እያሻሸ እንጂ እንደ ቋረኛው ካሳ ጎራዴ አያወዛውዝም። ከታላቁ የኦሮሚያ አመፅ ጋር በተያያዘ “በሚናገራቸው ንግግሮች” ግን ስሜቱን መቆጣጠር የተቸገረ ይመስላል። ዞረም ቀረ አባይ ፀሃዬ እና ጓደኞቹ የገጠማቸውን ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት መጣራቸውን ቀጥለዋል። ይሳካላቸው ይሆን?
በአጤ ሃይለስላሴ ዘመን ገጣሚ ዮፍታሄ ንጉሴ እንዲህ ቋጥሮ ነበር፣
ወላድ ኢትዮጵያ - ምጥ ይዟታል አሉ!
ማርያም! ማርያም! በሉ 

Thursday, December 31, 2015

ህወሓት እንዴት ሰነበተ?ከተስፋዬ ገብረአብ

የህወሓትን የጓዳ ወግ ማወቅ አስቸጋሪ የነበረበት ዘመን እንደዋዛ አልፎአል። ዛሬ ቀዳዳቸው በዝቶ፤ ቴክኖሎጂውም አግዞ የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ያሰቡትም በቀላሉ ይገኛል። ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። መረጃ ከሌለ ምንም ነገር የለም። ለችግሮች መፍትሄም አይገኝም። ወያኔ ዛሬ በአስር ሺዎች ኦሮሞዎችን በገፍ የሚያስረው ስለ ቄሮ በቂ መረጃ ስለሌለው መሆኑ ይታወቃል። ተቃዋሚ የፖለቲካ ተንታኞች ወይም የማህበራዊ ድረገፅ ፀሃፊዎች አንዳንድ ጊዜ አስቂኝ ስህተት ይሰራሉ። ማለትም ሳያውቁ ለወያኔ የሚጠቅም መረጃና ምክር ይፅፋሉ። የወያኔ የፀጥታ ቢሮ መረጃዎችን እየመዘነ ወደ ጥቅም የሚለውጥ የተደራጀ ክፍል አለው። እንዲህ ያለው ማርሽ ቀያሪ ዘመን ብቅ ሲል ጊዜና መረጃን በጥንቃቄ መጠቀም ካልተቻለ ወርቃማ እድል ሊያመልጥ ይችላል። በመሆኑም በዚህ አጭር መጣጥፍ አንዳንድ ጠቋሚ ነጥቦችን ብቻ በጨረፍታ አነሳለሁ። ለመሆኑ ሃይለማርያም መንግስት እንዴት ሰነበተ?

Friday, December 18, 2015

ጎዳናው የት ያደርሳል?ተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

አባይ ፀሃዬ ስልጣኑን ከመለስ ዜናዊ ከተረከበ ወዲህ የመጀመሪያው ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ከሰላሳ ቀናት በፊት ጀልዱ ተባለች ትንሽ መንደር ላይ የተለኮሰው ቁጣ እና አመፅ መላ ኦሮሚያን አጥለቅልቆታል። ይህን ፅሁፍ ከማተሜ በፊትም አመፁ ከኦሮሚያ አልፎ ወደ ምእራብ ጎንደር የተስፋፋ ሲሆን፤ የወያኔ ቡድን የገጠመውን ፈተና በምን አይነት ዘዴ ማፈን እንደሚችል ሲመክር መሰንበቱ እውነት ነው። ይቻላቸው ይሆን? የሚቻልበትም ሆነ የማይቻልበት እድል አለ።

Friday, January 30, 2015

የኦሮሚያ ደራስያን ማህበር (OWA)

በውጭ አገር የሚገኙ መፅሃፍ ያሳተሙ ኦሮሞዎች OWA (Oromia writers Association) ለማቋቋም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሰሞኑን ወሬ ሰማሁ። አሳቡን አልጠላሁትም። በርግጥ “የአፍሪቃ ቀንድ ደራስያን ማህበር” ቢሆን ይመረጥ ነበር። ትልቁ ጃንጥላ እስኪዘረጋ አነስተኛዎቹን መጠቀም ግን ክፋት የለውም። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የአማርኛ ፀሃፊዎችን ብቻ የሚያገለግልና የሚያበረታታ በመሆኑ የOWA መቋቋም አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም። እዚህ ላይ ግን በጥብቅ ማንሳት የምፈልገው አሳብ አለ። ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማ እንደ ቀዳሚ የኦሮሚያ ፀሃፊዎች መጠን ስማቸውና ስራቸው በማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ መካተት ይኖርበታል።